ዓመት በፊት በሸኽ ሙሐመድ ሳኒ ሃቢብ እና በሸኽ ሰይድ ሙሐመድ ሳዲቅ ወደ አማርኛ ቋንቋ ተተርጉሞ የቀረበው የክቡር ቅዱስ ቁርኣን የአማርኛ ትርጉም፤ በወንድም ሙሐመድ ፈረጅ ድምፅ ተዘጋጅቶ በተለያዩ አጋጣሚዎች የቅዱስ ቁርኣንን ትርጉም ማድመጥ ለሚፈልጉ አመቺ ኾኖ ቀርቧል።
ሥራው ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ በቅርቡ በዚህ መተግበሪያ እስኪጫን ድረስ፤ ለጊዜው ሱረት አል ፋቲሃን ጨምሮ ከሱረቱ አን ናስ እስከ ሱረቱ አን ነበእ (አንድ ጁዝ) የትርጉም ድምፅ ሥራው ያለክፍያ ቀርቧል።
አጋጣሚ እንደ አላህ ፈቃድ ሥራችንን ከእንከን የጠራ ለማድረግ በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜትና ጥንቃቄ ጥረት ያደረግን ቢኾንም፤ ነንና ልንሳሳት እንደምንችል እናምናለን። ይህ ሥራ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚሸጋገር የቅዱስ ቁርአን ትርጉም እንደመኾኑ በማድመጥም ኾነ በማንበብ ሂደት ውስጥ የሚታያችኹን ክፍተት እንድተጠቁሙን በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን።
ታላቅ ሥራ አኑረው ያለፉ አባቶቻችንንና ከህትመት እስከ ስርጭት የደከሙ ወንድምና እህቶችን ኹሉ ለሠሩት መልካም ሠራ ምንዳውን ያብዛላቸው። በሰማነው የምንጠቀም ያድርገን። !!